Fana: At a Speed of Life!

ት/ቤት ሀገር ተረካቢ ትውልድ የምንሰራበት ትልቅ ተቋም ነው – ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ቤት ቀጣዩን ሀገር ተረካቢ ትውልድ የምንሰራበት ትልቅ ተቋም በመሆኑ ያለምንም ልዩነት በጋራ ልንረባረብ ይገባል ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ትምህርት ለትውልድ በሚል መሪ ሐሳብ የሚካሄደው የትምህርት መሰረተ ልማት ማሻሻያ ንቅናቄ በሶማሌ ክልል ዛሬ ተጀምሯል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፣ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ፣ የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አብዱላሂ አብዲን ጨምሮ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል፡፡

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በመርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ዓላማ የተበላሸውን የትምህርት ስርዓት ለመጠገን ነው ብለዋል፡፡

አሁን የተጀመረው ንቅናቄ ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት መፍትሔ እንደሚሰጥም ነው ገለጹት፡፡

የትምህርት ጥራትን የማሻሻል ተግባር በመንግስት ብቻ ስለማይከናወን ሁሉም ሰው ትምህርት ቤቶችን መደገፍ ከቻለ የሚፈለገውን ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል አስገንዝበዋል፡፡

አቶ ሙስጠፌ በበኩላቸው÷ ከለውጡ በኋላ ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ የትምህርት ቤቶች ማስፋፊያ እና ግንባታ በንቃት እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል፣ የፈተና ስርቆትን እና ኩረጃን ለመግታት ተጨባጭ ሥራዎች ተከናውነዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር እያከናወነ ያለው የትምህርት ማሻሻያ እንቅስቃሴ መቀጠል ያለበት ተግባር ስለመሆኑም አመላክተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.