ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሕይወታቸውን ላጡ በ’ሌኒንግራድ ጀግኖች ተከላካዮች መታሰቢያ ሐውልት’ የአበባ ጉንጉን አኖሩ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ሕይወታቸውን ላጡ በ’ሌኒንግራድ ጀግኖች ተከላካዮች መታሰቢያ ሐውልት’ ላይ የአበባ ጉንጉን አኖሩ፡፡
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሁለተኛው የሩሲያ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ ለመሳተፍ ሩሲያ-ቅዱስ ፒተርስበርግ ከተማ መግባታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
“ለሰላም ደኅንነትና ልማት” በሚል መሪ ሐሳብ በሚካሄደው ጉባዔ ላይ 49 የአፍሪካ ሀገራት ይሳተፋሉ፡፡
ለሁለት ቀናት የሚቆየው ጉባዔ ዓላማም÷ የሩሲያ-አፍሪካን ትብብር ማሳደግ መሆኑ ተመልክቷል፡፡
በተጨማሪም የአፍሪካ መንግስታትን ሉዓላዊነት ማጠናከር የጉባዔው ዓላማ ስለመሆኑ ተገልጿል፡፡
ከጉባዔው ጎን ለጎንም የሩሲያ እና አፍሪካን ኢኮኖሚያዊ እና ሰብዓዊ ጉዳዮች የሚመለከቱ ፎረሞች ይደረጋሉ ነው የተባለው፡፡