የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት 6ኛ የምርጫ ጊዜ 2ኛ የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል፡፡
ጉባኤው በሁለት ቀናት ቆይታው የ2015 በጀት የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች፣ የኦዲት፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ ቤትና የም/ቤቱን እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያዳምጣል።
በተጨማሪም የ2016 የክልሉን የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅድና የማስፈጸሚያ በጀት መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡
ጉባኤው በአዋጆችና በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመወያየት ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡