Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ (ኢ/ር) ከቮልስዋገን ኩባንያ የአፍሪካ ከፍተኛ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ

 

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ (ኢ/ር) እና ምክትል ኮሚሽነር ዳንኤል ተሬሳ ከጀርመኑ ቮልስዋገን የመኪና አምራች ኩባንያ የአፍሪካ ከፍተኛ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ።

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ከጀርመን አምባሳደር ስቴፈን አውር ጋር በአውቶሞቲቭ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ላይ እየተደረጉ ስላሉ ዘርፈ ብዙ ማሻሻዎች ላይ ምክክር ማድረጋቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል።

መንግስት በተለይም በአውቶሞቲቭ ኢንቨስትመንት ዘርፍ ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ተመራጭ መዳረሻ እንድትሆን ፍላጎት እንዳለውም በዚህ ወቅት ገልጸውላቸዋል።

በተጨማሪም እንደ ቮልስዋገን ያሉ ዓለም አቀፍ አምራቾች በዘርፉ እንዲሳተፉ እና እንዲያለሙ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.