Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለጤና፣ ለግብርና እንዲሁም ለኃይል አቅርቦት ዘርፎች መጠቀም ትፈልጋለች – በለጠ ሞላ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለጤና፣ ለግብርና እንዲሁም ለኃይል አቅርቦት ዘርፎች መጠቀም እንደምትፈልግ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ተናገሩ።
ሚኒስትሩ ከሩሲያው የአቶሚክ ኤነርጂ ኤጀንሲ ዋና ኃላፊ አሌክሴይ ሌካቼቭ ጋር በኢትዮጵያ ለሚተገበረው የኒውክሌር ልማት ፍኖተ ካርታ ስምምነት ተፈራርመዋል።

በርዱስ ፒተርስበርግ ከተማ እየተካሄደ ከሚገኘው የሩሲያ አፍሪካ ጉባኤ ጎን ለጎን የተፈረመው የአሁኑ የአፈጻጸም ሰነድ ከዚህ ቀደም የተፈረመውን ስምምነት ወደ ተግባር ለማስገባትና በዘርፉ ግልፅ አሰራርን ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

የሩሲያው የአቶሚክ ኤነርጂ ኤጀንሲ ዋና ኃላፊ አሌክሴይ ሌካቼቭ በስምምነቱ ወቅት እንዳሉት፣ በአቶሚክ ሳይንስ ላይ የኢትዮጵያውያን ባለሙያዎችን አቅም መገንባት የስምምነቱ ቀዳሚ ትኩረት መሆኑን አንስተዋል።
ተቋሙ በ8 ሃገራት 33 የኒውክሌር ምርምር ማዕከላት ግንባታ ላይ እየሰሩ እንደሆነ አንስተዋል።

ዛሬ በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ለስምምነት የበቃው የኒውክሌር ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ፍኖተ ካርታ ኢትዮጵያ በዘርፉ የህክምና፣ የግብርና፣ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦትና በምርምር ላይ ያላትን አቅም ለማዘመን ያስችላታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.