Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል በ24 ቢሊየን ብር ወጪ 6 ሺህ 81 ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 በጀት ዓመት በኦሮሚያ ክልል 6 ሺህ 81 ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በቢሮው የእቅድና በጀት ዝግጅት ዳይሬክተር ሃሰን እንድሪስ÷ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ደረጃውን የጠበቀ ትምህርት ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት መሰራቱን ተናግረዋል፡፡

በተለይም የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል እና አስፈላጊ የትምህርት ግብዓቶችን ለማሟላት በቅንጅት ተሰርቷል ነው ያሉት፡፡

በዚህ መሰረት በበጀት ዓመቱ በሕዝብ ተሳትፎ 6 ሺህ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶችን ለመገባንት ታቅዶ 6 ሺህ 81 ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን ነው የገለጹት፡፡

ለግንባታው 24 ቢሊሊየን ብር ወጪ መደረጉን ጠቁመው÷ ለዚህም ባለሃብቶችን እና ሕብረተሰቡን አመስግነዋል፡፡

ግንባታቸው ከተጠናቀቁ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 5 ሺህ 955 የሚሆኑት አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን አቶ ሀሰን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

በመላኩ ገድፍ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.