የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለወዳጅነት ጨዋታ አሜሪካ ገባ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለወዳጅነት ጨዋታ አሜሪካ ገብቷል፡፡
ዋልያዎቹ በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት ያረፉ ሲሆን÷ በሚቀጥሉት ቀናት ልምምድ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአሜሪካ ቆይታው ሐምሌ 26 በዋሽንግተን ዲሲ ከጋያና ብሔራዊ ቡድን እናሐምሌ 29 በሳውዘርን ክረሰንት ስታዲየም ከአትላንታ ሮቨርስ ለመጫዎት ቀጠሮ መያዙ ይታወሳል።