በደቡብ ክልል ለሕዝቡ የሚገባውን ልማት ለማቅረብ እየተሰራ ነው ተባለ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሕዝቡ የሚገባውን ልማት ለማቅረብ እየተሰራ እንደሚገኝ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የከተማ እና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ ተስፋዬ ይገዙ ተናገሩ፡፡
አቶ ተስፋዬ ትምህርት ለትውልድ በሚል መሪ ሐሳብ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት የግንባታ ስራ በወላይታ ሶዶ ከተማ አስጀምረዋል፡፡
ሕብረተሰቡን በማሳተፍ የሊንታላ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታ እስከሚጠናቀቅ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚደረግ ጠቁመዋል፡፡
የወላይታ ሶዶ ከተማ የልማት ግስጋሴን ለማሳለጥ የትምህርት አቅርቦት አስፈላጊ ነው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!