Fana: At a Speed of Life!

በቻይና ውሃን ከተማ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተከፍተዋል

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና ውሃን ከተማ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተከፍተዋል።

ከሶስት ወራት በላይ ተዘግተው የቆዩት ትምህርት ቤቶች ዳግም ተከፍተው ተማሪዎችም ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰዋል።

ወደ ትምህርት ገበታቸው የተመለሱት የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎችና የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ናቸው ተብሏል።

ፈተናው በኮሮና ቫይረስ ተፅዕኖ ሳቢያ ይሰጥበት ከነበረው ጊዜ ተራዝሞ ከቀጣዩ ሃምሌ ወር ጀምሮ ይሰጣል ነው የተባለው።

ወደ ትምህርት ገበታቸው የተመሰሉ ተማሪዎች የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የወጡ መመሪያዎችን በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

እድሜያቸው ከ10 አመት በታች የሆኑ በሚሊየን የሚቆጠሩ ህጻናት ግን በዚህ አመት ወደ ትምህርት ገበታቸው ላይመለሱ ይችላሉ ነው የተባለው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.