ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ሁለት የውጭ ሀገር ተጨዋቾችን አስፈረመ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ሁለት የውጭ ሀገር ተጫዋቾችን ለሁለት ዓመት ኮንትራት ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡
ክለቡ ናይጀሪያዊው ሞሰስ ኦዶ ቶቹኩን እና ጋናዊውን አማካይ ክዋሜ አዶምን ማስፈረሙን የክለቡ መረጃ ያመላክታል፡፡
ኦዶ ቶቹኩ በሀገሩ ናይጄሪያ፣ ግብፅ፣ ኢራን፣ ሳይፕረስ፣ ሱዳን እና ቻይና ሊግ ረዘም ያለ የእግር ኳስ ሕይወት ማሳለፉ ተገልጿል፡፡
ጋናዊው የ26 ዓመት የተከላካይ አማካይ አዶም ፍሪምፓንግን በስዊድኑ ዳልኩርግ ክለብ እንዲሁም በሀገሩ ክለቦች አሻንቲኮቶኮ እና አዱዋና ስታር መጫወቱ ተጫውቶ አሳልፏል።
ሁለቱም ተጫዋችች ዛሬ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በመገኘት ለሁለት ዓመት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሚያቆያቸውን ፊርማ አኑረዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!