ህንድ ለዩክሬን ግጭት ሁሉን አቀፍ መፍትሄ እንዲሰጥ ጠየቀች
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ህንድ ለዩክሬን ግጭት ሁሉን አቀፍ መፍትሄ እንዲሰጥ ጠየቀች።
በሳዑዲ አረቢያ በተካሄደው ስብሰባ፥ ኒው ዴልሂ የውይይት እና የዲፕሎማሲ አስፈላጊነትን አንስታለች።
በሳምንቱ መጨረሻ በዩክሬን ጉዳይ ሳዑዲ ባስተናገደችው የሰላም ውይይት ላይ የተገኙት የህንድ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አጂት ዶቫል፥ ኒው ዴልሂ ግጭቱን ለማስቆም ብቸኛው አማራጭ ውይይት እና ዲፕሎማሲ ነው ብላ እንደምታምን ገልጸዋል።
አጂት ዶቫል ህንድ ለችግሩ ሰላማዊ እና ዘላቂ መፍትሄ ለማግኘት ያላትን ቁርጠኝነትም ማረጋገጣቸው ተመላክቷል።
የዩክሬን ግጭት በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለይም በዓለም ደቡባዊ ክፍላተ ሀገራት ያሳደረው ተፅእኖ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
ከዚህም የተነሳ ህንድ ለዩክሬን ሰብአዊ ዕርዳታ እንደምታቀርብ እና በደቡብ ላሉ ጎረቤቶቿ ደግሞ ኢኮኖሚያዊ ዕርዳታ እንደምትሰጥ ባለስልጣኑ መናገራቸውን አር ቲ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!