ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሩዋንዳ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቀጥሎ ባለው የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን የማጠናከር ስራ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሩዋንዳ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ቪንሴንት ቢሩታን ዛሬ ጠዋት በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
በውይይታቸውም ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ በ1970ዎቹ መገባደጃ ላይ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ከጀመሩ በኋላ ጠንካራ እና ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ የሁለትዮሽ ትብብር መፍጠራቸውን ገልፀዋል።
በዚህ ጊዜ ውስጥም በርካታ የሁለትዮሽ የትብብር ስምምነቶች በተለያዩ ዘርፎች ተፈራርመዋል ብለዋል።
ከውይይታቸውም ቀጥሎ ችግኞችን በአንድነት ፓርክ አብረው መትከላቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።