Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ ከህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የልማት አጋርነት አስተዳደር ረዳት ፀሀፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ ከህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የልማት አጋርነት አስተዳደር ረዳት ፀሀፊ ከሆኑት አቢላሻ ጆሺ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው የህንድ ቴክኒካል እና ኢኮኖሚ ትብብር ፕሮግራምን በኢትዮጵያ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር አድርገዋል።

በዚህ ወቅት ረዳት ፀሀፊዋ አቢላሻ ጆሺ ÷ የህንድ ቴክኒካል እና ኢኮኖሚ ትብብር ፕሮግራምን በኢትዮጵያ ስልጠና የሚሰጣቸውን ባለሙያዎች ቁጥር በየዓመቱ እየጨመረ መምጣቱን ገልፀዋል፡፡

አምባሳደር ደመቀ በበኩላቸው ÷ የህንድ መንግስት በየአመቱ ከ400 ለሚበልጡ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የስልጠና መርሃ ግብር ማዘጋጀት በመቻሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከህንድ ጋር በአቅም ግንባታ ዘርፍ በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ ናት ማለታቸውን ከህንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በህንድ የቴክኒካልና ኢኮኖሚ ትብብር ፕሮግራም በኢትዮጵያ የኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ማኔጅመንት፣ የውሃ ሀብት፣ ኢነርጂ፣ አይሲቲን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የክህሎት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.