Fana: At a Speed of Life!

በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች በሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር የተጠረጠሩ 387 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች በሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ተሳትፈዋል የተባሉ 387 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው÷ በሀገሪቱ ቀደም ሲል 521 ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀሎች ይፋ ተደርገዋል፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውሩ የተሳተፉ 387 ግለሰቦች ከዓለም አቀፍ የሕግ አስከባሪ ድርጅቶች ጋር በመተባበር  በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አመላክቷል፡፡

በሕገ ወጥ ገንዘብ አዘዋዋሪዎች ሲንቀሳቀስ የነበረ ከ4 ቢሊየን ድርሃም በላይ ገንዘብ በመንግስት መወረሱን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡

የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ም/ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሌ/ጄ ሼክ ሳይፍ ቢን ዛይድ አል ናህያን÷ሕገ ወጦችን ለመቆጣጠር የተወሰደውን እርምጃ አድንቀዋል፡፡

እርምጃው  የሀገሪቱን ብሄራዊ ደህንነትከማስጠበቅ ባለፈ በእድገት ጎዳና ላይ የጀመረችውን ጉዞ ለማስቀጥ ል ሚናው ከፍተኛ ነው ማለታቸውን  ገልፍ ቱ  ዴይ  ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.