Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ ተቋማት የኮቪድ19 ወረርሽኝን ከመከላከል ጎን ለጎን ሙስናን መከላከል ላይ ትኩረት ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳሰበ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 30 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንግስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ከመከላከል ጎን ለጎን ተያይዘው የሚመጡ የሙስና ተግባራትን መከላከል ላይ ሊዘናጉ እንደማይገባ የፌደራል ጸረ ሙስና ኮሚሽን አሳሰበ።

መንግስት ህዝቡን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተከሰተው የኮቪድ19 ወረርሽኝ ለመከላከል በሁሉም መስክ ትኩረቱን ወደዛው አድርጓል።

ምንም እንኳን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ተጨማሪ ችግር እንዳይሆኑ ስራዎች እየተሰሩ ቢሆንም የመንግስትን በእነዚህ ጉዳዮች ላይ መወጠር የተመለከቱ አካላት ወደ ግላዊነታቸው ፊታቸውን ማዞራቸው አይቀርም።

የፌደራል ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ዛሬ ያወጣው መረጃም ይህንን ያመላክታል።

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ወዶ አጦ ህገ ወጥ የመሬት ወረራ፣ የገቢ አሰባሰብና የፋይናንስ ተቋማት አካባቢ ችግሮች መስተዋላቸውን ጠቁመዋል።

በዳሰሳው ባቀረበው ግኝትም የጤናው ዘርፍ መዘናጋት እንደሌለበት የፋይናንስና ህገ ወጥ መሬት ወረራ ችግሮች እንደተስተዋለባቸው አንስቷል።

ስለዚህ የሚመለከታቸው ተቋማት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉም ኮሚሽኑ አሳስቧል።

በገቢ አሰባሰብ ላይም ተገቢ ያልሆነ ገቢ መተመንና ላልተገባ ድርድር መዳረግ እንዲሁም የፍትሀዊ ቀረጥ አሰባሰብ ችግርና የግብር ስወራ በዳሰሳው ችግር ሆነው ተለይተዋል።

እነዚህንና መሰል መነሻ ነጥቦችን የዳሰሰው ኮሚሽኑ አሁን ላይ የሚደረጉ የሙስና ተግባራት ከመቼውም ጊዜ በላይ የከፉ ተደርገው የሚወሰዱ ናቸው ብሏል።

ችግሮቹን ከስር ከስር እየተከታተለ እንደሚያስተካክልና ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድባቸው እንደሚያደርግ ያነሳው ኮሚሽኑ ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

በሃይለኢየሱስ ስዩም

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.