Fana: At a Speed of Life!

74 ቤቶችና 160 ተሽከርካሪዎች ሲታገዱ 156 ሚሊየን ብር በላይ ደግሞ በመንግስት ተወርሷል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 በጀት ዓመት 689 ሚሊየን ብር፣ 74 መኖሪያ ቤቶች፣ አንድ ሕንጻና 160 ተሽከርካሪዎች ሲታገዱ 156 ሚሊየን ብር በላይ ደግሞ በመንግስት መወረሱን የፍትሕ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቀው÷በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የመንግስትና የሕዝብን ጥቅም በማስጠበቅ ረገድ በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡

በዓመቱ በተካሄደ የሃብት ምርመራ ስራም 689 ሚሊየን ብር፣ 74 መኖሪያ ቤቶች፣ አንድ ሕንጻና 160 ተሽከርካሪዎች መታገዳቸው ተገልጿል፡፡

ከዚህ ባለፈም 137 ሺህ 556 ካሬ ሜትር ይዞታ እና 3 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ አክሲዮኖች መታገዳቸው ነው የተመላከተው፡፡

በሌላ በኩል 130 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር፣ የዋጋ ግምታቸው 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሆኑ ሁለት ተሽከርካሪዎች እና 10 ሚሊየን ብር የሚያወጡ ሁለት መኖሪያ ቤቶች በመንግስት መወረሳቸው ተገልጿል፡፡

1 ነጥብ 0221 ኪሎ ግራም የሆነ ወርቅም ውርስ የተደገ ሲሆን÷ ለብሄራዊ ባንክ ተሽጦ 3 ነጥብ 17 ሚሊየን ብር ለመንግስት ገቢ መደረጉም ተጠቁሟል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.