Fana: At a Speed of Life!

ኮንትሮባንድን ለመከላከል የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር ውጤት ማስመዝገቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኮንትሮባንድ እና ሕገ-ወጥ ንግድን ለመከላከል በአምስት ተቋማት የተጀመረው ቅንጅታዊ አሰራር ውጤት ማስመዝግቡ ተገልጿል

የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ካሳሁን ጎፌ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት÷ ኮንትሮባንድ በሀገራት የውጭ ንግድ ተወዳዳሪነት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡

በኮንትሮባንድ ንግድ ለሀገር ሰላምና ደህንነት አደጋ የሚሆኑ ጦር መሳሪያዎች በስፋት እየተዘዋወሩ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

ድርጊቱን ለመከላከል በ5 ተቋማት የተጀመረው ቅንጅታዊ አሰራርም በሞያሌ በኩል ሲወጣ የነበረው የጥራጥሬ እህል እንዲቀንስ ማድረጉን አንስተዋል፡፡

የፍትሕ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፍቃዱ ጸጋ በበኩላቸው÷የቅንጅት ስራው ለረጅም ዓመታት ሲንከባለሉ የመጡ የክስ መዝገቦች እልባት እንዲያገኙ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

የኮንትሮባንድ ንግድ ተዋናዮች ለጊዜው ቢሰወሩም ከሕግ ውጪ እንደማይሆኑ የገለጹት ደግሞ
የጉሙሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ናቸው፡፡

ወንጀለኞችን በሕግ ጥላ ስር ለማዋል ጠንካራ አደረጃጀት ተፈጥሯል ያሉት ኮሚሽነሩ ÷ ኮንትሮባንድን ለመከላከል አስፈላጊው ግብዓት ለማሟላት ይሰራል ብለዋል፡፡

በአልማዝ መኮንን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.