Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ በጅግጅጋ የተከሰተው የእሳት አደጋ ተጎጂዎች መልሶ ማቋቋምና ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ በጅግጅጋ ከተማ አዲሱ ታይዋን የገበያ ማዕከል ተከስቶ በነበረው የእሳት አደጋ ከተቋቋመው የተጎጂዎች መልሶ ማቋቋምና ደጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ።

ርዕሰ መስተዳደሩ በውይይቱ ላይ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ አዲሱ ታይዋን ተብሎ በሚጠራው የገበያ ማዕከል በደረሰው የእሳት አዳጋ ላይ የተካሄደው የጥናት ውጤት ሪፖርትን አዳምጠዋል፡፡

በጅግጅጋ ከተማ ታይዋን ገበያ በተከሰተው የእሳት አደጋ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለተጎጂዎች ሀብት ለማሰባሰብ የሚያስችል መድረክ እየተካሄደ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም የሶማሌ ተወላጆች በሚገኙባቸው የአፍሪካ ሀገራት ለተጎጂዎች መቋቋሚያ ሀብት ለማሰባሰብ የተለያዩ መድረኮች እንደሚዘጋጁ መገለጹን የክልሉ መገኛኛ ብዙሀን መረጃ ያመላክታል፡፡

እስካሁን በተጎጂዎች መልሶ ማቋቋምና ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ የተሰበሰበው ገንዘብ በእሳት አደጋው ለተጓዱ ነጋዴዎች እንዲሰጥ አቅጣጫ እንደተሰጠም ተገልጿል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.