የኒውክሌር ሳይንስ ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ዓላማ ለመጠቀም እየተሰራ ነው ተባለ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ ሀብት ከቴክኖሎጂው ዕድገት ጋር በማላመድ የኒውክሌር ሳይንስ ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ዓላማ ለመጠቀም እየተሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አታወቀ፡፡
ከተለያዩ ሚኒስቴሮች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የኢትዮጵያ የኒውክሌር ፕሮግራም ዐውደ ጥናት ተካሂዷል፡፡
በዐውደ ጥናቱም በሀገሪቱ የኒውክሌር ቴክኖሎጂ ግንባታ ምንነት፣ አስፈላጊነት እና የወደፊት ተስፋዎች እንዲሁም የዘርፉ አምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ምክክር ተደርጓል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር የኢኖቬሽንና ምርምር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ዶ/ር)÷ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ዓላማ ለማዋል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁንና ከሩሲያ መንግስት ጋር አብሮ ለመስራት መፈራረማቸውን አስታውሰዋል፡፡
በኢትዮጵያ የኒውክሌር ሳይንስ ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ዓላማ ለመጠቀም የመጀመሪያ ደረጃ ላይ እንገኛለን ማለታቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
በኢትዮጵያ ጠንካራ የኒውክሌር ቴክኖሎጂ ዘርፍ ለመመስረት ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂ ነድፈን ወደ ተግባር ገብተናል ብለዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!