የህዝብ አንገብጋቢ ችግሮችን ለመፍታት ውጤታማ ስራ እየተሰራ ነው – አቶ አደም ፋራህ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ አንገብጋቢ ችግሮችን ለመፍታት ውጤታማ ስራ እየተሰራ መሆኑን የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የጽህፈት ቤት ኃላፊ አደም ፋራህ ገለጹ፡፡
የክህሎት መር የስራ እድል ፈጠራና የኑሮ ውድነት ማረጋጋት ልዩ እቅድ ያለፉት 3 ወራት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩም ፥ የፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊዎች፣ የክልል ንግድ ቢሮ ኃላፊዎች እንዲሁም የክልል ስራ እድል ፈጠራ ቢሮ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
አቶ አደም ፋራህ በዚህ ወቅት እንዳሉት ፥ በስራ እድል ፈጠራና በኑሮ ውድነት ቅነሳ ላይ የሚሰሩ ስራዎች በፓርቲና በመንግስት ቅንጅት እንዲሰራ የተፈለገው የህዝብ አንገብጋቢ ጥያቄዎች ስለሆነ ነው።
ብልጽግና ፓርቲ ሰው ተኮር ፓርቲ እንደመሆኑ የህዝብ አንገብጋቢ ጥያቄዎች የፓርቲውም አንገብጋቢ ጥያቄ መሆናቸውን ጭምርም ነው ያነሱት።
እነዚህን የህዝብ ጥያቄ ቶሎ ምላሽ ማግኘት እንዲችሉ የፖለቲካ አመራሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚጠበቅበትም ገልፀዋል፡፡
ባለፉት ወራት በተጨባጭ የመጡ ለውጦችና የተመዘገቡ ውጤቶች ከፍላጎቱ ስፋት አንፃር በቂ ነው ማለት ስለማይቻል የበለጠ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባም ነው ያስገነዘቡት።
ስለሆነም ከስራ እድል ፈጠራና ከኑሮ ውድነት መረጋጋት ጋር ተያይዞ የተያዙ ግቦችን በውጤታማ ለማሳካት እና ጥራትና ዘላቂነትን ለማረጋገጥ መፍጠንና መፍጠር ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።
መንግስት ከታክስ ያገኝ የነበረውን ከ12.4 ቢሊዮን ብር በላይ በመተው ከቀረጥ ነፃ በፍራንኮ ቫሉታ የምግብ ሸቀጦች እንዲገባ መፍቀዱን የገለጹት ደግሞ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ገ/መስቀል ጫላ ናቸው፡፡
በዚህም ገበያውን በማረጋጋት ምርቶቹ ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርቡ መደረጉን መናገራቸውን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በተጨማሪም የተባባሰ ሁኔታ እንዳይፈጠር መንግስት ለማዳበሪያ መግዣ ከ21 ቢሊየን ብር በላይ ድጎማ በማድረጉ ቀጣይ ዓመት የምርቶች ዋጋ እንዳይንር በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ጠቅሰዋል፡፡
#Ethiopia #Prosperityparty
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!