Fana: At a Speed of Life!

መሪዎች ከታሪክ ተወቃሽነት ለመውጣት በጋራ መሥራት ይገባናል – አቶ አረጋ ከበደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መሪዎች ከታሪክ ተወቃሽነት ለመውጣት በጋራ መሥራት ይገባናል ሲሉ አዲስ የተሾሙት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ፡፡

የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በዓለ ሲመት ተካሄደ ሲሆን ፥ ለቀድሞው ርዕሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) እና ካቢኒያቸውም ደግሞ አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል።

በበዓለ ሲመታቸው ላይ ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ጥሪውን ተቀብለው ለመጡ እንግዶች ሁሉ ምሥጋና አቅርበዋል።

የአማራ ሕዝብ ለሀገር ግንባታ ያለውን አስተዋጽኦ ተረድታችሁና አሁን ላይ ያለውን ችግር አውቃችሁ በመምጣታችሁ ክብር ይገባችኋል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

የሀገር መከላከያ ሠራዊት ለሀገር በተለይም ለአማራ ክልል ሕዝብ እያደረገው ላለው አስተዋጽኦና ተጋድሎ ምሥጋና ይገባዋልም ነው ያሉት።

አክለውም ፥ ሕዝብን ከአደጋ ለማላቀቅ የውስጥ ችግራችንን መፍታት ይገባናል ብለዋል።

አጣቃሽና እንደየሁኔታው የምንቀያየር ፖለቲከኞች በመሆናችን ችግሮችን መፍታት አልቻልንም ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ፥ ገቢራዊ ሥራ ባለመሥራታችን ችግር ውስጥ ቆይተናልም ብለዋል።

የክልላችንን ችግሮች በተደጋጋሚ ተነጋግረንባቸዋል ብለውም ፥ በተግባር ችግሮችን ካልፈታን ሕዝባችንን ለአደጋ እናጋልጣለን ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በቁርጠኝነት ለምናደርገው እንቅስቃሴ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጎናችን እንድትሆኑ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

በፓርቲው የጋራ ዓላማና ጥቅም በመነሳት በጋራ መሥራት ይገባል ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ፥ ከዚያ ውጭ ያለው አካሄድ አዋጭ አለመሆኑንም አመላክተዋል።

ከዚህ በኋላ ችግር የሚያስተናግድ አቅም የለንም ያሉት አቶ አረጋ ፥ ችግሮቻችንን ካልፈታን ሀገርና ሕዝብ አደጋ ላይ እንጥላለንም ነው ያሉት።

አክለውም ፥ ከታሪክ ተወቃሽነት ለመውጣት በጋራ መሥራት ይገባናልም ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ በየደረጃው ያሉ መሪዎች ለሕዝብ ጥቅም እንዲሠሩና ሕዝብን እንዲያሻግሩም ጥሪ አቅርበዋል።

#Ethiopia #Amhara #Ethiopianregions

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.