የአፍሪካ – ሲንጋፖር የንግድ ፎረም እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ – ሲንጋፖር የንግድ ፎረም በሲንጋፖር እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮምሽነር ለሊሴ ነሜ (ኢ/ር) እና የኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አሰፈጻሚ አክሊሉ ታደስ በፎረሙ ላይ እየተካፈሉ ነው፡፡
ኮሚሽነሯ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ሃሳብ ፥ የአፍሪካ ሲንጋፖር የቢዝነስ ፎረም በአፍሪካ እና እስያ መካከል ያለውን የንግድ እና የኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማጠናከር ቁልፍ መድረክ እንደሆነ አንስተዋል።
አክለውም ፥ በቆይታቸው በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎት ካላቸው ከ17 በላይ የሲንጋፖር ባለሃብቶች ጋር ውጤታማ ቆይታ ማድረጋቸውንም ነው የተናገሩት።
በዚህም ባለሃብቶቹ ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ እና እምቅ የኢንቨስትመንት እድሎችን እንዲመለከቱ ግብዣ እንዳቀረቡላቸው ጠቅሰዋል፡፡
ፎረሙ ከዛሬ ጀምሮ ለሦሥት ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡