Fana: At a Speed of Life!

ፍሎሪዳ የመሬት መንሸራተት ባስከተለ ኃይለኛ አውሎ ንፋስ መመታቷ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፍሎሪዳ የመሬት መንሸራተት ባስከተለ ኃይለኛ አውሎ ንፋስ መመታቷ ተሰምቷል፡፡

“ኢዳሊያ” የተሰኘው ይኸው አውሎ ንፋስ የፍሎሪዳን ነዋሪዎች ሕይወት ሥጋት ላይ እንደጣለና ፍጥነቱም 201 ኪሎ ሜትር በሠዓት ሆኖ እንደተመዘገበ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የፍሎሪዳው ገዢ ሮን ዴሳንቲስ ÷ ኃይለኛው አውሎ ንፋስ ወደ ባሕር ሲነፍስ የውሃ አካላትን እስከ 4 ነጥብ 8 ሜትር ከፍታ ወደ ላይ ሊያነሳ እንደሚችልና አንዳንድ አካባቢዎችም በውሃ ማዕበል ሊመቱ እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡

የግዛቷ አንዳንድ አካባቢዎች ፣ ከተሞች እና መንገዶች ከጉልበት በታች በሚሸፍን ጎርፍ መጥለቅለቅ መጀመራቸውም በዘገባው ተመላክቷል፡፡

በአውሎ ንፋሱ የሚደርሰውን ውድመት ለመጠገን ከ40 ሺህ በላይ ሠራተኞች የክስተቱን ማብቃት በተጠንቀቅ እየተጠባበቁ ነው ተብሏል፡፡

ሮን ዴሳንቲስ ÷ መሠረተ-ልማቶች በወደሙባቸው አካባቢዎች ዜጎች ከወዳደቁ የኤሌክትሪክ መሥመሮች እንዲጠነቀቁ አሳስበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.