ከክልሉ ተወላጅ ዳያስፖራዎች ጋር ውጤታማ ውይይት መካሄዱን የሶማሌ ክልል አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ፣ እንግሊዝና ኬንያ ከሚኖሩ የሶማሌ ክልል ተወላጅ ዳያስፖራዎች ጋር ባሳለፍነው ወር ያካሄድናቸው ውይይቶች ስኬታማ ናቸው ሲሉ የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳደር ኢብራሂም ኡስማን ገለጹ፡፡
አቶ ኢብራሂም ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን እንደገለጹት÷ ውይይቶቹ ከዳያስፖራ አባላቱ ጋር ያለውን ትስስር ለማጠናከር ያለሙ ናቸው፡፡
በተጨማሪም በክልሉ በተለያዩ የልማትና ኢንቨስትመንት ስራዎች ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማስቻል ያለሙ መሆናቸውን ነው የተናገሩት፡፡
የውይይቱ ተሳታፊ ዳያስፖራዎችም ከክልሉ ጋር ተቀራርቦ በመስራት በልማትና ኢንቨስትመንት ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ተሳታፎ ለማሳደግ ከፍተኛ መነሳሳት ማሳየታቸውን ጠቁመዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!