Fana: At a Speed of Life!

በግብዓት እጥረት ተቋርጦ የነበረው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ስራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በግብዓት እጥረት ምክንያት ላለፉት ሶስት ሳምንታት ተቋርጦ የነበረው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ስራ መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡

ማዕከሉ በአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ፣ በዳግማዊ ሚኒልክ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና በየአብ ሜዲካል ሴንተር ኤንድ ሪሃብሊቴሽን በሦስትዮሽ ስምምነት ውል እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

የኩላሊት እጥበት ማዕከሉ ቦሶስቱ ተቋማት ድጋፍና በሌሎች አጋር ድርጅት ያላሰለሰ ጥረት በዛሬው ዕለት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.