Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ የካቢኔ አባላት ከሽሮሜዳ-ቁስቋም እየተሰራ ያለውን የመንገድ ፕሮጀክት ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ እና የካቢኔ አባላት ከሽሮሜዳ-ቁስቋም እየተሰራ ያለውን የመንገድ ፕሮጀክት ጎበኙ፡፡

ኢንጅነር ታከለ ኡማ በጉብኙቱ ወቅት እንደገለጹት ልማት የሁሉንም ጥረት፤የሁሉንም ብርታት የሚጠይቅ ሂደት መሆኑን ጠቅሰው ለሁላችንም ጥቅም ሲባል ፈተናዎች ሲኖሩ በጋራ የምንሻገራቸው ናቸው ብለዋል።

ከሽሮሜዳ-ቁስቋም እየተሰራ ባለው የመንገድ ፕሮጀክት መሳካት የንግድ ሱቃችሁን እና መኖሪያ ቤታችሁ እንዲፈርስ ለፈቀዱ ሁሉ የጋራ ጥቅምን ስላስቀደማችሁ ከልብ ማመስገን እወዳለው ሲሉ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ምስጋናቸው አቅርበዋል።

ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የመንገድ ፕሮጀክቱን በቅርቡ አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት ክፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.