Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ ለሱዳን እና ሶማሊያ 10 ሺህ ኪሎ ግራም የህክምና ቁሳቁሶችን አጓጓዘ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሱዳን እና ሶማሊያ የኮቪድ19 የህክምና ቁሳቁሶችን አጓጓዘ።

አየር መንገዱ 7 ሺህ ኪሎ ግራም የህክምና ቁሳቁስ ለሱዳን እንዲሁም 3 ሺህ ኪሎ ግራም የህክምና ቁሳቁስ ደግሞ ለሶማሊያ አጓጉዟል።

የህክምና ቁሳቁሶቹ ሃገራቱ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያደርጉትን ጥረት ለማገዝ የሚውሉ መሆኑን ከአየር መንገዱ ያገገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አየር መንገዱ ከዚህ ቀደም ከጃክ ማ ፋውንዴሽን የአፍሪካ ሃገራት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያደርጉትን ጥረት ለማገዝ ተበረከቱ የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶችን ለበርካታ የአፍሪካ ሃገራት ማድረሱ ይታወሳል።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.