Fana: At a Speed of Life!

ብሪታንያ ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የ5 ነጥብ 9 ሚሊየን ፓውንድ ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሪታንያ መንግስት ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የ5 ነጥብ 9 ሚሊየን ፓውንድ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉ በብሪታንያ ቀይ መስቀል እና በኔዘርላንድስ ቀይ መስቀል ማህበር የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚታገዝ ተመላክቷል፡፡

ድጋፉ በጤና፣ ንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እና ንጽሕና አጠባበቅ ላይ ትኩረት ላደረጉ ፕሮጀክቶች የሚውል ነው ተብሏል።

ለፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ የስምምነት ሰነድ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ፕሬዚዳንት አበራ ቶላ እና በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ዳረን ዌልሽ መካከል ተፈርሟል።

ከተደረገው ድጋፍ ውስጥ 3 ነጥብ 4 ሚሊየን ፓውንዱ በገንዘብ የቀረበ ሲሆን÷ ቀሪው ደግሞ ለቴክኒክ ድጋፍ የሚውል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከ5 ነጥብ 9 ሚሊየን ፓውንዱ በተጨማሪ ፕሮጀክቱን ለማገዝ የሚያገለግሉ 10 ተሸከርካሪዎች ድጋፍ ተደርጓል፡፡

በፍቅርተ ከበደ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.