Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በመኸር እየለማ ካለው መሬት 160 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይጠበቃል – ቢሮው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በመኸር አዝመራ እየለማ ካለው መሬት ከ160 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ድረስ ሳህሉን (ዶ/ር)  ጨምሮ ሌሎች አመራሮች በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ የለማን የማሽላ ሰብል ጎብኝተዋል፡፡

ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት÷ የሰብል ምርቱ የሚሰበሰበው በክልሉ በመኸር ወቅት ከሚለማው ከ5 ሚሊየን ሄክታር የሚበልጥ መሬት ላይ ነው፡፡

የታቀደውን ምርት ለማግኘት ለአርሶ አደሩ ሙያዊ ድጋፍ በመስጠት የተጠናከር የአረምና የተባይ ቁጥጥር ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የበረሃ አንበጣን ጨምሮ የስንዴ ቢጫ ዋግ፣ ግሪሳ ወፍና ተምች የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ቀድሞ መከላከል መቻሉን ገልፀዋል፡፡

በክልሉ የመኸር ሰብል ያለበትን ሁኔታ በመስክ መልክታ በማየት ክፍተቱን ለመሙላትና ጥንካሬውን ለማስቀጠል በቅንጅት እንደሚሰራ ጠቁመው÷ አርሶ አደሩ ማሳውን በየቀኑ በማሰስ ከአረምና ከተባይ እንዲጠብቅ አሳስበዋል፡፡

ከመኸር ሰብል ልማቱ በተጓዳኝ ምርታማነትን ለማሳደግ በቀሪ እርጥበትና በበጋ መስኖ የተሻለ ምርት ለማግኘት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ መናገራቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

 

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.