የብልፅግና ፓርቲ የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘ከዕዳ ወደ ምንዳ’ በሚል መሪ ሐሳብ ለብፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የተዘጋጀው የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ዛሬ በአዳማ ከተማ ተጀምሯል።
በስልጠናው ላይ ከሁሉም ክልሎች የተወጣጡ ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ነው።
የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አደም ፋራህ እንደገለጹት፤ የስልጠናው ዓላማ÷ ከፍተኛ አመራሮች ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን ተገንዝበው ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር ፓርቲው ለሕዝቡ የገባውን ቃል ማስፈፀም የሚያስችል የአመራር አቅም እንዲፈጠር ነው፡፡
ፓርቲው ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋጥ በሚያደርገው ትግል የአመራሩ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ወሳኝ ነው ማለታቸውን የብልጽግና ፓርቲ መረጃ ያመላክታል፡፡
በየደረጃው ያሉ አመራሮችን በስልጠና አቅም የመገንባት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል፡፡
ስልጠናው ከዛሬ ጀምሮ ለ11 ቀናት እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!