በአዲስ አበባ ዛሬ ትምህርት ተጀምሯል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁሉም ትምህርት ቤቶች ትምህርት መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
በሌላ በኩል በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን እንደሚጀመር ይጠበቃል፡፡
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቡበከር አዶሽ በሰጡት መግለጫ÷ በአስተዳደሩ መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም ትምህርት እንደሚጀመር አስታውቀዋል፡፡
ለዚህም ትምህርት ለመጀመር የሚያስችሉ የተለያዩ የዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውንም ነው የገለጹት፡፡
ለአብነትም የትምህርት ቤቶችን ዕድሳት፣ የማሻሻያ ሥራዎች እንዲሁም በመምህራን ዝግጅት ረገድ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል፡፡
እንዲሁም በ2015 ዓ.ም የነበሩ ችግሮችን በመገምገምና በማረም ለ2016 የትምህርት ዘመን የተሻለ ዝግጅት መደረጉን ጠቁመው÷ መምህራንም የትምህርት ሥብራቱን በሚጠግን ሁኔታ በበቂ ዝግጅት ላይ የተመሠረተ ትምህርት እንዲሰጡ ጠይቀዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!