Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖር ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተባበሩት መንግስታትድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አቶ ደመቀ ከ78ኛው የተመድ ጠቅላላ የመሪዎች ጉባዔ ጎን ጎን በጸጥታው ምክር ቤታ ማሻሻያ ትግበራ ዙሪያ የጀርመኑ ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ ባዘጋጁት ውይይት ላይ ተሳትፈዋል፡፡

ውይይቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰቱ ወቅታዊ ሁኔታዎችና በተመድ የማሻሻያ ስራዎች ላይ ሃሳብ ለመለዋወጥ ያለመ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

አቶ ደመቀ÷ ሀገራት በተመድ የጸጥው ምክር ቤት ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖራቸው ማድረግ የመላው ዓለም ፍላጎት መሆኑን አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያም በጉዳዩ ላይ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር ተመሳሳይ አቋም እንዳላት ጠቁመው÷ ምክር ቤቱ ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖረው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የታቀደውን ዘላቂ ልማትና እድገት እንዲያሳኩ አስቸኳይ ማሻሻያ ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

በሌላ በኩል አቶ ደመቀ÷ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.