የኢትዮጵያ እና አየርላንድን ግንኙነት ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደረገ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እና የአየርላንድን ግንኙነት ማሳደግ በሚቻልበት አግባብ ላይ ውይይት ተደረገ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 78ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን ከአየርላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚሼል ማርቲን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም የኢትዮጵያ እና የአየርላንድን የሁለትዮሽ ግንኙነትን ማደስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
የሰላም ስምምነቱ በትክክለኛው አቅጣጫ እየሄደ መሆኑን አቶ ደመቀ በውይይታቸው ላይ ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘውን የመልሶ ግንባታ እና መልሶ ማቋቋም ሥራም አየር ላንድ እንድትደግፍም ጠይቀዋል፡፡
የአየርላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚሼል ማርቲን በበኩላቸው÷ ለሁለቱም ሀገራት ሕዝብ ተጠቃሚነት ሀገራቸው እንደምትሠራ ጠቅሰዋል፡፡
በተመሳሳይ ከኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ መሃመድ አብድረሃማን አልታኒ ጋር ውጤታማ ውይይት ያደረጉት አቶ ደመቀ፤ ኢትዮጵያ ከኳታር ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ እንደምታጠናክር ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ለኳታር ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ እንደሆነች ተናግረዋል።
የኳታር ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት የጋራ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ እያደገ መምጣቱን ጠቅሰዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!