Fana: At a Speed of Life!

ከሚያራርቁን ድርጊቶች በመራቅ ለአሰባሳቢ ሁኔታዎች መትጋት ይገባል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እርስ በእርሳችን ከሚጋጩና ከሚያጠራጥሩ ድርጊቶች ርቀን በፍቅርና በአንድነት በመኖር እንደ ደመራ አሰባሳቢ ጥበብን ልንገበይ ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባ አዳነች ለ2016 ዓ.ም የደመራ እና የመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም÷ የመስቀል በዓልን ስናከብር እርስ በእርስ በመዋደድ፣ ከማይረቡ ጉዳዮች እርስ በእርሳችን ከሚጋጩና ከሚያጠራጥሩን ሐሳቦችና ድርጊቶች ርቀን መሆን አለበት ብለዋል፡፡

አክለውም በፍቅር እና በአንድነት በመኖር እንደ ደመራ አሰባሳቢ ጥበብን እየገበየን በዓሉን ማክበር ይኖርብናል ብለዋል፡፡

ሁላችንም ለከተማችን እና ለሀገራችን ሰላምና ልማት ደመራችንን እንደምር ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

በተያያዘም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ለክርስትና እምነት ተከታዮች ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም÷ በአንድነት ኢትዮጵያን የማበልፀግ ዓላማ እና ተግባራችን ሳይለያይ በትጋት ልንሠራ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.