Fana: At a Speed of Life!

የታክስ ሕግ ተገዢነት የንቅናቄ መድረክ በሐዋሳ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን የታክስ ሕግ ተገዢነት የንቅናቄ መድረክ በሐዋሳ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡

የንቅናቄ መድረኩ እየተካሄደ የሚገኘው “ግብር ለሀገር ክብር” በሚል መሪ ሐሳብ ነው፡፡

በመድረኩ ላይ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ የክልሉ አመራሮች፣ በየደረጃው የሚገኙ የዘርፋ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝቷል።

የባለስለጣኑ ኃላፊ ኃይሉ ጉዱራ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የክልሉን ወጪ ከ60 በመቶ በላይ ለመሸፈን በያዝነው በጀት ዓመት 13 ነጥብ 13 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ እየሠራን ነው ብለዋል፡፡

ለዕቅዱ መሳካትም ሁሉም አካል በቅንጅት እንዲሠራ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በብርሃኑ በጋሻው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.