Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት ያላት ልምድ ለማላዊ ዓይነተኛ ግብዓት ነው – የማላዊ ኤምባሲ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት በአጭር ጊዜ ያካበተችው ልምድ ለማላዊ ኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት ዓይነተኛ ግብዓት መሆኑን በኢትዮጵያ የማላዊ ኤምባሲ ገለጸ፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የትራንስፎርሜሽንና ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ኃላፊ ፍፁም ከተማ በኢትዮጵያ ከማላዊ ኤምባሲ ተወካይ ኢቫንስ ቺሳሱላ ጋር መክረዋል፡፡

በውይይታቸውም ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባትና በማልማት ያላት ልምድ ማላዊ ለምታስበው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታና ልማት አይነተኛ ግብዓት እንደሚሆን ኢቫንስ ቺሳሱላ ገልፀዋል።

ኮርፖሬሽኑ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባት፣ በማልማት እና በማስተዳደር ያካበተውን ልምድ መሰረት በማድረግ በማላዊ የሚታሰበውን ልማት እውን ለማድረግ ግብዓት የሚሆኑ ዝርዝር ጉዳዮችንም አንስተዋል፡፡

በዘርፉ ከማላዊ መንግስት ጋር ለመስራት ከስምምነት መደረሱን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

የማላዊ ልዑክ የሐዋሳ እና ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ን ጎብኝቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.