Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በቱርክ የደረሰውን የሽብር ጥቃት በጽኑ አወገዘች

አዲስ አበባ፣ መሰከረም 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአንካራ የቱርክ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ላይ የደረሰውን የሽብር ጥቃት በጽኑ አውግዟል።

ሚኒስቴሩ፥ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ጸሎታችን ለተጎጂዎች እና ለሟች ቤተሰቦች ነው ብሏል።

መሰል ጥቃት ምንም ዓይነት ምክንያት የለውም፥ በኢትዮጵያውያን ሽብርተኝነት ምንም ቦታ ስለሌለው እነዚህን አረመኔያዊ ድርጊቶች በማውገዝ አንድ ሆነን ቆመናል ሲል ገልጿል።

በዚህም ከቱርክ ህዝብና መንግስት ጋር ነን ሲል ሚኒስቴሩ በትዊተር ገጹ ባወጣው መረጃ አመልክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.