Fana: At a Speed of Life!

የየም ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል ‘ሄቦ’ ተከበረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የየም ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል ‘ሄቦ’ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል የመጡ የብሔረሰቡ ተወላጆች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ምሁራን በተገኙበት በሳጃ ከተማ ተከብሯል፡፡

በዕለቱም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ዞን ምስረታ መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

የየም ብሄረሰብ የራሱ ቋንቋና የቀን መቁጠሪያ ያለው ሲሆን የዘመን መለወጫ በዓሉም የይቅርታና እርቅ፣ የአብሮነትና የአንድነት ተምሳሌት እንዲሁም የመልካም ምኞት መግለጫ ሆኖ ለዘመናት በብሄረሰቡ ዘንድ ሲከበር ቆይቷል።

የየም ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ገብረ ሚካኤል በዚሁ ጊዜ እንዳሉት÷ ‘ሄቦ’ በዓል መንግስት ለዘመናት የቆየውን የማህበረሰቡን በዞን እንዲደራጅ ጥያቄ ምላሽ በሰጠበት ማግስት መከበሩ ልዩ ያደርገዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አፈ ጉባኤ ፋጤ ሱርሞሎ በበኩላቸው÷ የየም የማንነት መገለጫዎችን የማሳደግና የመንከባከብ ሂደቱ የጋራ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ መሰረት መሆኑን ገልጸዋል።

በሙክታር ጠሃ እና በተስፋሁን ከበደ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.