Fana: At a Speed of Life!

የተልባ ጥቅሞች በጥቂቱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ተልባ በለስላሳና ገንቢ ጣዕሙ ይታወቃል፤ ይህም በተለያዩ የምግብ አሰራሮችን በመጠቀም ለጤና የሚያስፈልግን ንጥረ ነገሮች ማግኘት ይቻላል፡፡

ተልባ በተለያዩ ንጥረ -ነገሮች የበለጸገ ነው፡፡ ይህም ካሎሪ፣ ካርቦሃይድሬት፣ ፋይበር፣ ስብ፣ ፕሮቲን፣ ማንጋኒዝ፣ ማግኒዢየም፣ ፎስፎረስ፣ ኩፐር፣ ቪታሚን ቢ6 እና ብረት ተልባን በንጥረ ነገር እንዲበለጽግ ካደረጉት ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ።

በተልባ ውስጥ ኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ በከፍተኛ መጠን ይገኛል።

ይህም ለልብ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፤ እባጭን ይቀንሳል ፤ ኮሌስትሮልን ይከላከላል፤ ዓይነት-2 የስኳር በሽታን ይከላከላል

ሁለገብ እና ለአጠቃቀም ቀላል የሆነው ተልባ የሰውነት ክብደትን ለመጠበቅ ይረዳል።

እነዚህን በርካታ የጤና ጥቅሞች ለማግኘትም በቀን 1 የሾርባ ማንኪያ (7 ግራም) የተፈጨ የተልባ እህል መጠቀም በቂ እንደሆነም ይነገራል፡፡

ሆኖም በቀን ከአምሰት የሾርባ ማንኪያ በላይ ተልባ ባይጠቀሙ ኽልዝላይን ይመክራል፡፡

የተልባ እህል በፋይበር የበለፀገ ሲሆን ፥ ከፍተኛ መጠን ተልባ መመገብ የምግብ መፈጨት ችግርን ያስከትላል። አልፎ አልፎ አለርጂ ሊያስከትልም ይችላል ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.