Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ምዕራብ ክልል በበጋ መስኖ ልማት 11 ሺህ ሄክታር በስንዴ ይሸፈናል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በ2016 በጀት ዓመት በ11 ሺህ ሄክታር የበጋ ስንዴ ለማምረት የዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተመለከተ፡፡

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) የውሃ አማራጮችንና የተፈጥሮ ማዳበሪያ ጭምር በመጠቀም የተሻለ ምርት ለመሰብሰብ ጥረት መደረግ አለበት ብለዋል።

የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችንና ሜካናይዜሽን ተግባራዊ በማድረግ የአርሶአደሩን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባም ነው የገለጹት፡፡

በበጋ የመስኖ ስንዴ የተሻለ ምርት ለማግኘት ከአካባቢው ሥነ- ምኅዳር ጋር ተስማሚ የሆነ የዘር አማራጭ መጠቀም እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

በዶሮ ጫጩትና የወተት ላም እርባታ የታየው መነቃቃት በሌሎች የሌማት ትሩፋት ስራዎች ላይ መጠናከር አለበት ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.