እሬትና ዘርፈ ብዙ ጥቅሞቹ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እሬት ለቆዳ ችግሮች ፍቱን የሚባል ዕጽዋት ቢሆንም ጥቅሙ ግን ከዚያም የላቀ ነው ሲሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ምርምራቸውን እንደቀጠሉ ነው፡፡
የጤና ችግሮች ሲከሰቱ መፍትሄ ናቸው ተብሎ በተለያዩ ምክንያቶች የሰሙትን ከመተግበርዎ በፊት የህክምና ባለሙያዎችን ማማከር ተገቢ እንደሆነ ይመከራል፡፡
ይሕም ተጨማሪ ለሆነ የጤና ችግር እንዳይጋለጡ ስለሚረዳም ነው፡፡
የቆዳ ችግር ካለብዎም እሬትን እንደመፍትሄ ከመውሰድዎ በፊት የቆዳ ህክምና ባለሙያዎችን ሃሳብ መጠየቅና ማማከር ይገባዎታል፡፡
የእሬት ጥቅሞች
• ለአነስተኛ የሰውነት ቃጠሎዎች፥ በየቀኑ እስከ ሦስት ጊዜ የእሬቱን ዝልግልግ ፈሳሽ (ጄል) የተጎዳው ቦታ ላይ በማድረግ ይጠቀሙ፣
• እሬት የፀሃይ ቃጠሎ ለማስታገስ የሚረዳ ቢሆንም ጥናቶች እንደሚሉት እሬት ፀሐይ ቃጠሎን ለመከላከል ያን ያህል ፍቱን እንዳልሆነ ያመላክታሉ፡፡ በዚህም በየቀኑ የፀሐይ መከላከያዎችን መቀባትዎንና ከጸሃይ ራስዎን መከላከል እንደሚገባ ይመከራል፡፡
• በትንሹ የመቆረጥ አደጋ ሲደርስ ቁስሉን በፍጥነት ለማዳን፣ ጠባሳ እንዳይኖር በማድረግና ባክቴሪያን ለመከላከል ይረዳል፡፡ በዚህም በቀን ሦስት ጊዜ መጠቀምዎን አይዘንጉ፣
• ቆዳን ለማለስለስ የእሬት ጄል ተመራጭ እንደሆነ ይነገራል፡፡ የደረቀ ቆዳን በማከም ቆዳዎን ለስላሳና ማራኪ ያደርጋል፣
• በቅዝቃዜ (በውርጭ) የተጎዳ የቆዳ ክፍልን ለማለስለስ፣
• ከአስም ጋር የተያያዘ ደረቅና የሚያሳክክ ቆዳን ለማስታገስ ይረዳል፣
• የቆረቆር እና የፎረፎር የቆዳ በሽታን ለማስታገስ ብሎም ለማከም ይጠቅማል፣
• ለብጉር ዓይነተኛ መፍትሄ ነው፡፡ በዚህም ብጉሩ የወጣበት ቦታ ላይ በየቀኑ ሦስት ጊዜ በመቀባት የቆዳዎን ጤና ይጠብቁ፡፡
ሆኖም እሬት ለቆዳዎ ሲጠቀሙ ማሳከክ ወይም ትንሽ የማቃጠል ስሜት ሊኖረው እንደሚችል ይገለጻል፡፡ ሆኖም ግን ሽፍታ ወይም ማደብደብ (መጉረብ) ዓይነት ካጋጠመዎት እሬቱን መጠቀምዎን ያቁሙ ሲሉም ይመክራሉ፡፡
በተጨማሪም ቆዳዎ ኢንፌክሽን ካለው ባለመጠቀም ኽልዝላይን ጥንቃቄ አድርጉ ይላል፡፡
እሬት የፀሃይ ቃጠሎ ለማስታገስ የሚረዳ ቢሆንም ጥናቶች እንደሚሉት እሬት የፀሐይ ቃጠሎን ለመከላከል ያን ያህል ፍቱን እንዳልሆነ ባለሙያዎች ያመላክታሉ፡፡ በዚህም በየቀኑ የፀሐይ መከላከያዎችን መቀባትዎንና ከጸሃይ ራስዎን መከላከል እንደሚገባዎ ይመከራል፡፡