Fana: At a Speed of Life!

5ኛው የኢሬቻ ፎረም እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 5ኛው የኢሬቻ ፎረም በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በመርሐ-ግብሩ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ የተለያዩ የሚኒስትሮች እና የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

ፎረሙ መስከረም 26 እና 27 ቀን 2016 ዓ.ም በሆረ ፊንፊኔ እና በሆረ ሀርሰዴ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓል አስመልክቶ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በፎረሙ የኢሬቻን እሴቶች የሚያንጸባርቁ የተለያዩ የጥናትና ምርምር ስራዎች መቅረባቸው ተገልጿል፡፡

በመራኦል ከድር

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.