Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መሰጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜኑ ግጭት ሳቢያ በትግራይ ክልል ተቋርጦ የቆየው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዛሬው ዕለት መሰጠት ጀምሯል፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ኪሮስ ግዑሽ (ዶ/ር) ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን 9 ሺህ 514 ተማሪዎች ይወስዳሉ፡፡

ከዚህ ውስጥም 6 ሺህ 513 ተማሪዎች የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ሲሆኑ ÷ 3 ሺህ 1 የሚሆኑት ደግሞ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ናቸው፡፡

ተማሪዎቹ በመቀሌ፣ በአክሱም፣ በአዲግራት እና በራያ ዩኒቨርሲቲዎች ነው የመልቀቂያ ፈተናውን እየወሰዱ የሚገኙት፡፡

ፈተናውን ከክልሉ እና ከትምህርት ሚኒስቴር የተዋቀረው ኮሚቴ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየሰጠ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.