Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ81 ሺህ በለጠ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 9 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ
ተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ81 ሺህ በለጠ ∶∶

በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 81ሺህ608 መድረሱን መረጃዎች ያሳያሉ∶∶

በዚህም ደቡብ አፍሪካ ሰፊውን ድርሻ ስትወስድ በሃገሪቱ14ሺህ335 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው 261 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

6ሺህ478 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ማገገም ችለዋል ነው የተባለው፡፡

እንዲሁም በግብፅ11ሺህ719 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 612 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገው 2ሺህ950 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል ፤ በአልጄሪያ 6ሺህ821 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው 3ሺህ409 ሰዎች ሲያገግሙ 542 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት መዳረጋቸው ታውቋል፡፡

በሞሮኮ 6ሺህ741 ሰዎች ፣በጋና 5ሺህ735 እና ካሜሮን 3ሺህ 105 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል ∶∶

በዚህም በአጠቃላይ በአፍሪካ 31ሺህ122 ሰዎች ሲያገግሙ 2ሺህ708 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

ምንጭ፡-africanews.com

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.