Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያሳድግ ጠየቁ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 29 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያሳድግ ጠየቁ፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኤሚ ኢ. ፖፕ ጋር ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅትም ድርጅቱ ኢትዮጵያ ፍልሰትን ለመቆጣጠር ለምታደርገው ጥረት የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያሳድግ ጠይቀዋል።

አቶ ደመቀ መኮንን አዲሷ ተሿሚ ኤሚ ኢ. ፖፕ በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በነበራቸው ቆይታም የኢትዮጵያ መንግስት ከድርጅቱ ጋር ጠንካራ አጋርነት ለመፍጠር ያለውን ፍላጎት ገልጸውላቸዋል።

በፕሪቶሪያው የሠላም ሥምምነት አተገባበር ላይ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፥ ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅትም ኢትዮጵያ የምታከናውነውን የሰፈራ እና የመልሶ ማቋቋም መርሐ-ግብር በመደገፍ ረገድ ቁልፍ ሚና እንዳለው አፅንዖት ሰጥተዋል።

ኤሚ ኢ. ፖፕ በበኩላቸው ÷ የአፍሪካ የፖለቲካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ የመጀመሪያ ጉብኝታቸውን መጀመራቸው ድርጅታቸው ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት ለመሥራት ያለውን ፍላጎት የሚያሳይ ነው ብለዋል።

አክለውም ድርጅቱ ኢትዮጵያ በምታከናውናቸው መልሶ ማቋቋም እና የመልሶ ግንባታ መርሐ-ግብር አጋር ለመሆን ቁርጠኛ እንደሆነ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.