Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በተያዘው በጀት ዓመት በተለያዩ ዘርፎች ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 134 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ መሰጠቱ ተገለፀ።

ባለሀብቶቹ የኢንቨስትመንት ፍቃድ የወሰዱት በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ፣ በኮንስትራክሽን፣ በትምህርት፣ በሆቴል፣ በነዳጅ ማደያ እና በገበያ ማዕከላት ዘርፍ ላይ ለመሰማራት እንደሆነ ተገልጿል።

የክልሉ የኢንዱስትሪና የኢንቨስትመንት ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ጋሻው ሸማ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ 134 ባለሀብቶች በየዘርፋቸው የካፒታል መነሻቸውና የሚፈጥሩትን የስራ ዕድል መጠን በየደረጃው በማስመዝገብ ነው የኢንቨስትመንት ፍቃድ እንዲወስዱ የተደረገው።

የኢንቨስትመንት ፍቃድ ከወሰዱ ባለሃብቶች መካከል ከ1 ቢሊየን 809 ሚሊየን ብር በላይ የመነሻ የካፒታል አቅም ያስመዘገቡ እና ከ30 ሺህ በላይ በቋሚና በጊዜያዊነት የስራ እድል ይፈጥራሉ ተብሎ የሚታሰቡ 107 ባለሀብቶች እንደሚገኙበት ታውቋል።

በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ደግሞ ከ503 ሚሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ለ 695 ዜጎች በቋሚና በጊዜያዊነት የስራ እድል ይፈጥራሉ ተብለው የታሰቡ 7 ባለሃብቶችም የኢንቨስትመንት ፍቃድ ከወሰዱት መካከል ናቸው ተብሏል።

በታሪክ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.