Fana: At a Speed of Life!

የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽንና ተመድ የውስጥ ተፈናቃዮችን ማቋቋም ላይ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተ/ማሪያም (ዶ/ር) ከተመድ ዋና ጸሃፊ የሀገር ውስጥ መፈናቀል ልዩ አማካሪ ሮበርት ፓይፐር ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ÷ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተባባሰ ከሚገኘውና በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ከሚከሰተው የውስጥ ተፈናቃዮች አያያዝ፣ ዘላቂ መፍትሄዎችና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የውስጥ ተፈናቃዮችን ለመደገፍና በዘላቂነት ለማቋቋም ከተመረጡ 15 የዓለም ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗ በውይይቱ ተነስቷል፡፡

ይህን ተከትሎም በጉዳዩ ላይ ተመድ ከኢትዮጵያ መንግስትና ከአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ጋር በትብብር ለመስራት መስማማቱን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.