Fana: At a Speed of Life!

ጉባዔው የበይነ-መረብ ተደራሽነት ክፍተትን መሙላት ላይ እንዲያተኩር ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባዔ የበይነ-መረብ ተደራሽነት ክፍተትን መሙላት ላይ እንዲያተኩር ኢትዮጵያ ጠየቀች፡፡

18ኛው ዓለም አቀፍ የበይነመረብ አስተዳደር ጉባዔ “ለምንፈልገው በይነ-መረብ ግንኙነት ሁሉንም ሰዎች ማብቃት” በሚል መሪ ሐሳብ በጃፓን ኪዮቶ ተካሂዷል፡፡

መድረኩ በተለያዩ የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ ሲመክር ቆይቶ መጠናቀቁን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ያደጉና በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት የበይነ¬-መረብ ተደራሽነት ከፍተኛ ልዩነት እንዳለ ገልጸዋል።

በምንፈልገው ሳይሆን ባለን በይነ መረብ ላይ ማተኮር ይኖረብናል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ፤ ስለምንፈልገው በይነ-መረብ ሀገራት እኩል ደረጃ ላይ ሲደርሱ እንነጋገራለን ብለዋል።

በመሆኑም የበይነ-መረብ ተደራሽነት ክፍተቱን መሙላት ላይ ትኩረት እንዲያደረግ አስገንዝበዋል።

አፍሪካውያን በጋራ የሚጠቀሙበት መሰረተ ልማት መዘርጋት፣ መረጃዎች (ዴታ) ደህንነቱ የተጠበቀና አስተማማኝ እንዲሆን ማድረግ፣ የወጣቶችን የዲጂታል ክህሎት ማሳደግ እና አዳዲስ የመፍትሄ ሐሳቦችን በጋራ ማልማትና መጠቀም ላይ በትብብር መስራት እንደሚጠበቅም ነው ያስገነዘቡት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.