Fana: At a Speed of Life!

የሰንደቅ ዓላማ ቀን በተለያዩ ክልሎች ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 16ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በተለያዩ ክልሎች “የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለህብረብሔራዊ አንድነታችንና ለሉዓላዊነታችን ዋስትና” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል፡፡

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቀኑ በተለያዩ ሁነቶች በቦንጋ ማዕከል ተከብሯል ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) እንደገለፁት ፥ ኢትዮጵያ ብዙ ቀለማት፣ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የሚገኙባት ሀገር ናት ብለዋል፡፡

ሆኖም በብሔር፣ በጎሳና በቋንቋ ቢለያዩም የጋራ የሚያደርጋቸው በርካታ እሴቶች እንዳሉም ነው የገለጹት።

ም/ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም ፥ ሰንደቅ ዓላማችን የሀገር ሉዓላዊነት መገለጫ፣ መከበሪያና ለሀገር ክብር ብዙዎች የተዋደቁበትና መስዋዕትነት የከፈሉበት ትልቁ መገለጫችን ነው ሲሉም ተናግረዋል ።

የድሮ አባቶቻችን ጠብቀው በክብር ባቆዩት ሰንደቅ ዓላማችን የኢትዮጵያ ህዝቦች ለሀገር ክብር በጋራ የሚቆሙበት፣ ለሀገር ዕድገት የሚወያዩበትና ጠላቶቻቸውን በጋራ የሚመከቱበት ጊዜ አሁን ነው ሲሉም ነው የገለጹት።

በተመሳሳይ አፋር ክልል በተለያዩ ሁነቶች የተከበረ ሲሆን ፥ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሀጂ አወል አርባ እና የአፋር ክልል ም/ቤት ዋና አፈ ጉባዔ አሲያ ከማል እንዲሁም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በአከባበሩ ላይ ተገኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድር ሀጂ አወል አርባ እንደገለፁት ፥ የሰንደቅ አላማ ቀን ሲከበር ቀደምት አባቶቻችን ሉአላዊነቷን ጠብቀው ያስረከቡን በመሆኑ ተተኪው ትውልድ የሀገሩን ሰላም ፣ አንድነትና ልማት ለማስጠበቅ ቃል የምንገባባበት ቀን ነው።

የአፋር ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ አሲያ ከማል በበኩላቸው ፥ ቀኑ ሲከበር የኢትዮጵያ የብልፅግና ጉዞና የጀመርነውን የለውጥ ጉዞ ወደ ማይቀለበስበት ደረጃ ለማድረስ በየጊዜው እያጋጠሙን ያሉ ችግሮችን በማስወገድ በአንድነትና በአብሮነት ስሜት የመንግስት የልማት እቅዶችን ለማሳካት በባንዲራችን ፊት ቃል የምንገባበት ቀን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በተመሳሳይ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ መሃመድ፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባዔ አያን አብዲ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የሀገር ሽማግሌዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ቀኑ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተከብሯል።

ርዕሰ መስተዳደሩ፥ የሀገር ሉዓላዊነት፣ የነፃነት፣ የአንድነትና የአብሮነት መገለጫ የሆነው ሰንደቅ ዓላማ ከፍተኛ መሰዋዕትነት የተከፈለበት በመሆኑ የሰንደቅ ዓላማን ክብር በመጠበቅ በዓለም አደባባዮች በኩራት እንዲውለበለብ ማድረግ የሁሉም ዜጎች ሀላፊነት ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዋል።

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አያን አብዲ በበኩላቸው፥ ሰንደቅ ዓላማ የሀገሪቱ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች አንድነት፣ ነፃነትና እኩልነት መገለጫ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ለሰንደቅ ዓላማ ተገቢውን ክብር ሊሰጥና ሊጠብቅ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.