ኢትዮጵያ በዓለም ምግብ ፎረም እየተሳተፈች ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ ዛሬ በተጀመረው የዓለም ምግብ ፎረም ላይ እየተሳተፈ ነው፡፡
በአረንጓዴ ልማት፣ በመስኖ ስንዴ ልማት ምርትና ምርታማነት እንዲሁም በሌማት ትሩፋት የተከናወኑ ተግባራትንና ተሞክሮዎችን የኢትዮጵያ ልዑክ በመድረኩ ላይ እንደሚያቀርብ ተመላክቷል፡፡
ከመድረኩ ጎን ለጎንም ከተለያዩ የዓለም አቀፍ የግብርና ምርምር ተቋማት፣ አኅጉርና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት እና መልኅቅ ድርጅቶች ጋር አብሮ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ልዑኩ እንደሚመክር ይጠበቃል፡፡
ፎረሙ ለአራት ቀናት ይቆያል መባሉን በሮም ኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡